የድሬዳዋ ልማት ማህበር የገቢ ማስገኛ G+7 ህንፃ የመሰረተ ድንጋይ በክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ሀምሌ 17/2015 ዓ/ም ተቀመጠ፡፡ የህንፃው ግንባታ 2 ዓመት እንደሚፈጅ የተገመተ ሲሆን የግንባታ ወጪውም ብር 230 ሚሊዮን እንደሆነ ታውቋል፡፡
የድሬዳዋ ልማት ማህበር ከኢተርናሽናል ሪፐብሊካን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የዜጎች ድምፅ መሰማትን፤ተጠያቂነትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ማረጋገጥ ለመልካም አስተዳደር ያለው ሚና በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ ከሀምሌ 25/2015 ዓ/ም ጀምሮ ለአራት ቀናት እያካሄደ ይገኛል።