የድሬዳዋ ልማት ማህበር ከድሬዳዋ ከተማ የወረዳ አመራሮች ጋር ልማት ማህበሩ ከመደገፍ አንፃር በጋራ መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመነጋገር በ19/06/2016 ዓ/ም በ ቢ ካፒታል ሆቴል የውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡
ውይይቱን የመሩት አቶ ሻኪር አህመድ የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ምክትል የጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆኑ እሳቸውም በንግግራቸው የወረዳ አመራሮች ከልማት ማህበሩ ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመመስረት የልማት እንቅስቃሴውን እንደ አንድ የስራ አካላቸው ቆጥረው ዕቅድ በማዘጋጀት፤አባላትን በማፍራት፤ከማህበሩ ጋር የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የተጀመረውን የልማት ተነሳሽነት ማስቀጠል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡